የብልጽግና መንግስት በተለያዩ የኦሮምያ ክልል መንደሮች ላይ የሰው አልባ/ደሮን በመጠቀም ያደረገው ጥቃት በርካታ የንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፎ ብዛት ያላቸውን አቁስሏል: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ- ጥር 1/2022

Published Jan. 4, 2022, 6:58 a.m. by FNN

313



የብልጽግና መንግስት በመላው ኦሮሚያ እና ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የጀመረውን ጦርነት በስፋት አጠናክሮ

ቀጥሎበታል። በዚህ ሰዓት ጦርነት የሌለበት አንድም የኦሮሚያ ክፍል የለም።በሰሞኑን ባደረገው ጦርነት

የብልጽግና መንግስት የድሮን እና የአየር ጥቃትን ብዙ ቦታዎች ላይ በመፈጸም በርካታ ንጹሐን ዜጎችን ለጉዳት

ዳርጓል። ከብዙ ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ቤት ንብረታቸው ባልተጠበቀ መጠን እና መልኩ

ወድሟል።ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በብልጽግና መንግስት ሃይሎች እና ተባባሪው የኤርትራ ሰራዊት ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድሮን እና አየር ጥቃት ተፈጽሞባቸው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የኦሮሚያ ክፍሎች መካከል

ካራዩ(ምስራቅ ሸዋ)፣ሐረርጌ( ሜኤሶ እና መቻራ አካባቢ)፣ የግንደበረት ደጋማ እና ቆላማ አካባቢዎች፣ሳላሌ፣ሜታ

ወልቅጤ እና ኪራሙ አካባቢዎች ጥቂቶቹ ናቸው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት እነዚህ የጥቃት ኢላማዎች

የሰላማዊ ዜጎች መኖርያ መንደር ከመሆናቸው የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።ይህ የብልጽግና ንጹሀን ዜጎችን እና

መኖርያ አካባቢዎችን ኢላማ ያደረገ የድሮን እና አየር ጥቃት የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ በፊትም በወሎ እና

ምእራብ ወለጋ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶችን አድርሷል። ይህ ንጹሐንን አና መኖሪያ አካባቢያቸውን ኢላማ ያደረገ

የብልጽግና መንግስት ወታደሮች ጥቃት ህዝቡ የእርስበርስ ጦርነትን ባለመደገፉ እየተበቀለ ነው።

የብልጽግና መንግስት በንጹሐን ዜጎች ላይ ድሮን እና የአየር ጥቃትን በመጠቀም እያደረሰ ያለውን ጥፋት እና ወንጀል

ኦነግ በእጅጉ ያወግዛል። የብልጽግና መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን እየፈጸመ መሆኑን እንገነዘባለን።

ስለሆነም የአለማቀፉ ማህበረሰብ ገለልተኛ በሆነ አካል በደረሰው ጉዳቱ ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ አሁንም በጽኑ

እንጠይቃለን።በተጨማሪም የአለማቀፉ ማህበረሰብ እና መንግስታት የብልጽግና መንግስት ከግብረ አበሮቹ ጋር

በመሆን ሕዝብ በሚበዛበት የአሮሚያ መንደርች ላይ የደሮን እና የአየር ጥቃትን በመፈጸም እያደረሰ ያለውን

ውድመት በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የፖለትካ እና ሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መፍትሔ የሚያገኙት በሰከነ እና ሀሉ አቀፍ የፖለቲካ

ውይይቶች እንጂ በጦርነት እና ንጹሐንን በአየር በመደብደብ እንደማይፈቱ ኦነግ በድጋሚ ያሳስባል።

ድል ለሰፊው ህዝብ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/

ጥር 1/2022


Similar posts:

𝐌𝐢𝐫𝐠𝐨𝐨𝐧𝐧𝐢 𝐁𝐮’𝐮𝐮𝐫𝐚𝐚 𝐁𝐚𝐤𝐤𝐚𝐚 𝐟𝐢 𝐘𝐞𝐫𝐨𝐨 𝐊𝐚𝐦𝐢𝐭𝐭𝐮𝐮 𝐊𝐚𝐛𝐚𝐣𝐚𝐦𝐮𝐮 𝐐𝐚𝐛𝐮.

A brief Political Manifesto of the OLF-OLA

OLF operations & drone attack in Oromia

Oduu Injifannoo WBO