;

የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ - ከፊውዳል አርስቶክራሲ እስከ አብዮታዊ ዲሞክራሲ

Published March 15, 2024, 4:01 p.m. by FNN in Amharic

የመጀመሪያ እትም መግቢያ

የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ በሚለዉ ርዕስ ላይ ለመፃፍ አስቤ የነበረዉ ከአዲስ አበባ ዩኒቬርስቲ የፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የትምህርት ክፍል ለመጀመሪያ ድግሪዬ ማሟያ ከተፃፈዉ ጽሑፍ ጊዜ ጀምሮ ነዉ፡፡ በዚያን ወቅት አማካሪዬ የነበሩት ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ፤ ይህ አርእስት ለመጀመሪያ ድግሪ ማሟያ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በስፋት ሊፃፍበትም የሚችል መሆኑን እንደምክርም እንደአስተያየትም በቃል ጣል አድርገዉልኝ የነበረዉን መሠረት በማድረግ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለመፃፍ ያደረብኝ ሐሳብ ከውስጤ ሳይጠፋ ቆይቶ የነበር ቢሆንም፤ ያጋጠሙኝ የሕይወት ውጣ ውረዶች እንኳን ጽሑፍ ማዘጋጀት ቀርቶ በሕይወት መኖር ራሱ ጥያቄ ምልክት ዉስጥ አስገብቶኝ ስለነበር ቅድሚያ አልተሰጠውም፡፡ በተለይ በደርግ መውደቂያ አከባቢ የነበሩ ሁኔታዎችና ቆይቶም ከ2001 እስከ መጋቢት 2002 ድረስ ለፊንጫኣ …ሙሉውን ያንብቡ


እውነት የኢትዮጵያ እምፓየር የመከላከያ ኃይል የሰላም አርበኛ ነው?

Published Jan. 1, 2024, 5:51 p.m. by Birhaanuu in Amharic


- ከArts Tv World ጋር የተደረገው የጀዋር መሃመድ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቅ -
በብርሃኑ ሁንዴ
Arts Tv World በሚባል ሚድያ ላይ በአቶ ደረጀ ኃይሌ ከኦቦ ጀዋር መሃመድ ጋር የተደረገውን ቃለ መጠየቅ ክፍል አንድ
አዳምጬ አንዳንድ ነገሮችን ታዘብኩኝ። ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት እስቲ ኦቦ ጀዋር ያላቸውን አንዳንድ ጥቂት ነገሮችን
ልጥቀስ፥
“የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመበላሸቱ የተነሳ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀረና አብዛኛው የፖለቲካ ስራ በመከላከያ ላይ
ወድቋል።
የኛ መከላከያ ዛሬ የአገር ውስጥ ጦርነትን ጠልቷል። ጀኔራሎቻችን መዋጋት በቃን እያሉ ነው።
ዛሬ ላይ ጦርነት የሚፈልግ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቪልም የለም፤ ባለ መለዮም የለም፤ ሚንስቴርም የለም። በጣም
እየቀነሰ መጥቷል።
ዛሬ No 1 የሰላም አርበኛ ወታደር ነው። ከወንድሞቹ ጋር መገዳደል …ሙሉውን ያንብቡ


በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የብሔሮች ብሔረሰቦች አስተያየት

Published May 16, 2022, 2:25 a.m. by FNN in Amharic

FNN ከቅማንቲ ማህበረሰብ ከአበባ ፤ከሲዳማ ማህበረሰብ ከዴንቦባ እና ከኦሮሞ ማህበረሰብ ከአብደታ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋል: ከእኛ ጋር ይቆዩ!ሙሉውን ያንብቡ


የምርጫ ቦርድ የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ አስተላልፎ የነበረውን ውሳኔ አሳድሶታል

Published March 29, 2022, 2:39 a.m. by FNN in Amharic

የኦነግ መግለጫ - መጋቢት 28/2022

የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ለአንድ አመት በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበሩትን የድርጅቱን ሊ/መንበር አቶ ዳውድ

ኢብሳን መጎብኘቱን አስመልክቶ ኦነግ በቀን 16/03/2022 መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የምርጫ

ቦርድ በ24/02/2022 ጠቅላላ ጉባኤን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ያስተላለፋቸውን ውሳኔ ኦነግ እንደደረሰዉ

ማሳወቅ እንወዳለን።

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እነዚህን አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ያስተላለፈው የኦነግ መሪዎች ያስገቡትን ቅሬታዎች እና

የፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ እንደሆነ አሳውቆናል።ይሁን እንጂ ኦነግ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ አመት በፊት

ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ መቀበላችንን አሳውቀን ነበር። የአሁኑ ውሳኔ ጥቅት መሻሻሎች ቢደረጉበትም ከአምናው

ውሳኔ ጋር አንድ መሆኑን ተገንዝበናል።

ኦነግ በህገወጥ መንገድ የተዘጉበት ጽ/ቤቶቹ እንዲከፈቱ ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የታሰሩ አባላቶቹ …ሙሉውን ያንብቡ


የብልጽግና መንግስት በተለያዩ የኦሮምያ ክልል መንደሮች ላይ የሰው አልባ/ደሮን በመጠቀም ያደረገው ጥቃት በርካታ የንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፎ ብዛት ያላቸውን አቁስሏል: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ- ጥር 1/2022

Published Jan. 4, 2022, 6:58 a.m. by FNN in Amharic

የብልጽግና መንግስት በመላው ኦሮሚያ እና ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የጀመረውን ጦርነት በስፋት አጠናክሮ

ቀጥሎበታል። በዚህ ሰዓት ጦርነት የሌለበት አንድም የኦሮሚያ ክፍል የለም።በሰሞኑን ባደረገው ጦርነት

የብልጽግና መንግስት የድሮን እና የአየር ጥቃትን ብዙ ቦታዎች ላይ በመፈጸም በርካታ ንጹሐን ዜጎችን ለጉዳት

ዳርጓል። ከብዙ ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ቤት ንብረታቸው ባልተጠበቀ መጠን እና መልኩ

ወድሟል።ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በብልጽግና መንግስት ሃይሎች እና ተባባሪው የኤርትራ ሰራዊት ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድሮን እና አየር ጥቃት ተፈጽሞባቸው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የኦሮሚያ ክፍሎች መካከል

ካራዩ(ምስራቅ ሸዋ)፣ሐረርጌ( ሜኤሶ እና መቻራ አካባቢ)፣ የግንደበረት ደጋማ እና ቆላማ አካባቢዎች፣ሳላሌ፣ሜታ

ወልቅጤ እና ኪራሙ አካባቢዎች ጥቂቶቹ ናቸው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት እነዚህ የጥቃት ኢላማዎች

የሰላማዊ ዜጎች …ሙሉውን ያንብቡ