የምርጫ ቦርድ የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ አስተላልፎ የነበረውን ውሳኔ አሳድሶታል

Published March 29, 2022, 2:39 a.m. by FNN
የኦነግ መግለጫ - መጋቢት 28/2022

የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ለአንድ አመት በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበሩትን የድርጅቱን ሊ/መንበር አቶ ዳውድ

ኢብሳን መጎብኘቱን አስመልክቶ ኦነግ በቀን 16/03/2022 መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የምርጫ

ቦርድ በ24/02/2022 ጠቅላላ ጉባኤን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ያስተላለፋቸውን ውሳኔ ኦነግ እንደደረሰዉ

ማሳወቅ እንወዳለን።

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እነዚህን አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ያስተላለፈው የኦነግ መሪዎች ያስገቡትን ቅሬታዎች እና

የፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ እንደሆነ አሳውቆናል።ይሁን እንጂ ኦነግ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ አመት በፊት

ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ መቀበላችንን አሳውቀን ነበር። የአሁኑ ውሳኔ ጥቅት መሻሻሎች ቢደረጉበትም ከአምናው

ውሳኔ ጋር አንድ መሆኑን ተገንዝበናል።

ኦነግ በህገወጥ መንገድ የተዘጉበት ጽ/ቤቶቹ እንዲከፈቱ ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የታሰሩ አባላቶቹ

ይፈቱ ዘንድ በተደጋጋሚ የምርጫ ቦርድን ሲጠይቅ ነበር። እንዲሁም የድርጅቱ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቁም

እስር ተለቀው እንደ ዜጋ መንቀሳቀስ እንዲችሉ እና የድርጅቱንም ተግባራት እንደ ማንኛውም ህጋዊ ፓርቲ መከወን

እንዲችሉ ጭምር ስናመለክት ነበር። በተጨማሪም ያለ አግባብ በህገወጥ መንገድ በገዥው ፓርቲ የጸጥታ ሀይሎች

የተዘረፉት የድርጅቱ ንብረቶች ማለትም ኮምፒውተሮች፣ የእጅ ስልኮች፣ሰነዶች እና ተሽከርካሪዎች እንዲመለሱልን

በተደጋጋሚ ስናመለክት መቆየታችን ይታወሳል።


Similar posts:

Ethiopia, A Failed State.

𝐌𝐢𝐫𝐠𝐨𝐨𝐧𝐧𝐢 𝐁𝐮’𝐮𝐮𝐫𝐚𝐚 𝐁𝐚𝐤𝐤𝐚𝐚 𝐟𝐢 𝐘𝐞𝐫𝐨𝐨 𝐊𝐚𝐦𝐢𝐭𝐭𝐮𝐮 𝐊𝐚𝐛𝐚𝐣𝐚𝐦𝐮𝐮 𝐐𝐚𝐛𝐮.

Mootummaan hooggantoota ABO seera malee mana hidhaatti dararaa jira

A brief Political Manifesto of the OLF-OLA